የፖሊሲ፣ ዕቅድና ፕሮጀክት ዝግጅትና ክትትል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ተጠሪነቱ ለኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ሆኖ ተግባሩ ከዚህ እንደሚከተለው ይሆናል፡፡
- የአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ልማት ስትራቴጂ ማስፈጸሚያ የሚሆኑ ዕቅድ እና ፕሮጀክት መቅረጽና መተግበር፣
- የአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ የልማት ችግሮች መለየትና ለመፍታት የሚያስችሉ ጥናቶችን ማካሄድና ለተጠቃሚዎች ማሰራጨት፣ አፈጻጸሙንም መከታተል፣
- ዕቅድና ፕሮጀክት አዘገጃጀትን በሚመለከት የስልጠና ማንዋሎችን ማዘጋጀትና ተግባራዊነታቸውን መከታተል፣
- የአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ሀገራዊ ስትራቴጂክና ዓመታዊ ዕቅድ ዝግጅት ሥራዎችን ማስተባበር፣ ማጠናቀርና ለሚመለከተው አካል በወቅቱ ማስተላለፍ፣
- የአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ የመካከለኛ ጊዜ ተንከባላይ እና የአንድ ዓመት የተጠቃለለ በጀት ማዘጋጀት፣ማጠናቀርና ለሚመለከተው አካል በወቅቱ ማስተላለፍ፣
- የዕቅድ አፈጻጸም ክትትልና ግምገማ ስልት መቀየስ፣ የወር፣ ሩብ ዓመትና ዓመታዊ የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ማዘጋጀት፣ መገምገምና ግብረ መልሶችን በማጠናቀር ለሚመለከታው አካላት ማስተላለፍ፣
- የዘርፉን ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ለማካሄድ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት በብቃት መፈጸም፣
- የአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ልማት ለመደገፍ የሚረዱ የሀብት ማፈላለጊያ ፕሮጀክቶችን ማዘጋጀትና ማፈላለግ፣
- የዘርፉን ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ለማካሄድ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት በብቃት መፈጸም፣
- የሥራ ሂደቱን የሥራ ዕቅድ ማዘጋጀት፣ አፈጻጸሙን መከታተል፣ ሪፖርት ማዘጋጀት፣
directorate list
1. የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር
የጽ/ቤት ኃላፊ እና (የዘርፉ ምክር ቤት አሰተባባሪ)
የስነ-ምግባር መከታተያ ክፍል
የህግ ክፍል
የውስጥ ኦዲት ዳይሬክቶሬት
የለውጥ ድጋፍ፣ ክትትል፣ የካይዘን ትግበራና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
2. የፖሊሲ፣ ዕቅድና ፕሮጀክት ዝግጅትና ክትትል ዳይሬክቶሬት
3. የሰው ኃብት ልማትና ስራ አመራር ዳይሬክቶሬት
5. የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
6. የሥርዓተ ፆታ እና ባለዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት