Mission , Vision and Values Mission , Vision and Values

ራዕይ

ለኢንዱስትሪው ልማት አስተማማኝና ሰፊ መሰረት ያለው ተወዳዳሪ የአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ

ልማት ተፈጥሮ ማየት፣

 

ተልዕኮ

የዘርፉን ልማት ለማፋጠን የሚረዱ ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎች፣ የድጋፍ ማዕቀፎችና ፕሮጀክቶች በማዘጋጀት፤

የአስፈፃሚና ባለድርሻ አካላትን የማስፈፀም አቅም በመገንባት፤ ውጤታማ መንግስታዊ ድጋፎችን እንዲቀርቡ

በማስተባበር እና በማመቻቸት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነ የአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ

ኢንዱስትሪ እንዲስፋፋ ማስቻል፤

የዘርፉ ልማት ዓላማዎች

  • በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ለከፍተኛ ኢንዱስትሪ ልማት ሰፊ መሰረት የሚጥሉ አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ

ኢንዱስትሪዎችን እንዲስፋፉ በማድረግ ፍትሃዊ ሃብት ክፍፍልን ማረጋገጥና ከግብርና መር ኢኮኖሚ ወደ

ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ የሚደረገውን ሽግግር ማፋጠን፣

  • የአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች ልማት ዘርፍ ተወዳዳሪ፣ ቀጣይነት ያለውና ለኢንዱስትሪው

ልማት ጠንካራ መሰረት የሚጥል እንዲሆን ድጋፍ የሚሰጡ ተቋማትን ማጠናከርና እንዲፈጠሩ መደገፍና

ማስተባበር፣

የሚሰጡ ድጋፎች

 

  • የማኑፋክቸሪግ ኢንዱስትሪ ልማት አቅም ግንባታ ስራዎች፣
  •  የኢንዱስትሪ ሥራ ፈጣሪነት አስተሳሰብና ክህሎት ልማት፣
  •  የኢንዱስትሪ መረጃ እና የምክር አገልግሎት፣(መዋዕለ ነዋያቸውን የሚያፈስቡት አዋጪ የሥራ ዘርፍ
  • መረጃ፣ የግብአት፣ የገበያ መረጃ…)
  • የኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንትን ለማሳደግ አዋጭነት ጥናት፣ የንግድ ሥራ ዕቅድ ዝግጅት፣
  • በካፒታል ሊዝ ፋይናንስ የኢንዱስትሪ ማሽነሪ አቅርቦት፣
  • የኢንዱስትሪ ክላስተርና መሠረተ ልማት አቅርቦት፣
  • የቴክኖሎጂ ልማትና ሽግግር፣
  • የኢንዱስትሪ ገበያ ልማትና ኢንዱስትሪዎች ትስስር መፍጠር፣(የገበያ መዳረሻን ማስፋት)
  • የኢንዱስትሪ የጥራት ደረጃና ምርታማነት የማሳደግ አሠራር፣ እና
  •  የኢንዱስትሪ የጥሬ ዕቃ ግብዓት አቅርቦት ትስስር መፍጠር፣