Updated and News Updated and News

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች ምርቶችን ወደ ውጭ ሀገራት በስፋት እንዲልኩ ለማድረግ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች ምርቶችን ወደውጭ ሀገራት በስፋት እንዲልኩ ለማድረግ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች ምርቶችን ወደውጭ ሀገራት በስፋት እንዲልኩ ለማድረግ አስፈላውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን አስታወቀ፡፡

 

በአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች የኤክስፖርት ማነቆዎችና መፍትሄዎች ዙሪያ መነሻ ሰነድ ቀርቦ ከአምራች ኢንተርፕራይዞች ጋር ምክክር ተካሂዷል፡፡

 

በምክክር መድረኩ ላይ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ጳውሎስ በርጋ እንደገለጹት ሀገራችን ካላት አቅምና #የተፈጥሮ_ጸጋ አንጻር ወደውጭ የምንልካው ምርቶች ዝቅተኛ መሆኑን አንስተዋል፡፡

 

ይህን ለመቀየርና አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች #ጥራት ያላቸው ምርቶችን በማምረት ወደውጭ ሀገራት በስፋት እንዲልኩ ተቋማቸው አስፈላጊውንና ተጨባጭ ድጋፍ ለማድረግ በአዲስ መልኩ መዋቀሩንና ዝግጁ መሆናቸውንም አስታውቀዋል፡፡

 

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱልፈታ የሱፍ በበኩላቸው #ኤክስፖርት ላይ የተሰማሩ አምራች ኢንተርፕራይዞች የሚያጋጥማቸውን ተግዳሮቶች ለመፍታት ከሚመለከታቸው አስፈጻሚና ባለድርሻ አካላት ጋር ተቀራርበው እንደሚሰሩና የኤክስፖርት ድርሻን ማሳደግ የተቋማቸው ዋነኛ ስራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

 

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ‹‹#የአምራች_ኢንተርፕራይዞች_አምባሳደር›› ሆኖ መስራቱን ይቀጥላል ያሉት አቶ አብዱልፈታ በዘርፉ የተሰማሩ አምራች ኢንተርፕራይዞች የሚያጋጥማቸውን ችግሮች በዘላቂነት ለመፍታት የአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች #ኤክስፖርት_ማህበር መመስረት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል፡፡

 

በመድረኩ የተሳተፉ አምራች ኢንተርፕራይዞች በበኩላቸው ተመሳሳይ መድረኮች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበው ከገበያ መረጃና መዳረሻ፣ ከውጭ ምንዛሬ፣ ከትራንስፖርትና ከብቃት የምስክር ወረቀት ጋር በተያያዘ የሚያጋጥማቸው ተግዳሮቶች እንዲፈቱላቸው ጠይቀዋል፡፡ 

 

በ2015 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች 6 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የሚያወጡ ምርቶችን ወደውጭ ሀገራት መላካቸው በውይይት መድረኩ ተገልጿል፡፡

Image