Updated and News Updated and News

አምራች ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ እንዲሆኑ የዘርፉ አስፈፃሚ አካላት በቁርጠኝነት መስራት ይገባቸዋል

አምራች ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ እንዲሆኑ የዘርፉ አስፈፃሚ አካላት በቁርጠኝነት መስራት ይገባቸዋል የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታ አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ
የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዞች ልማት ማቋቋሚያ ደንብ በሚኒስትሮች ምክርቤት ፀድቋል፡፡

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ በአዳማ ከተማ እየተሰጠ ያለውን የአቅም ግንባታ ስልጠና ሲከፍቱ እንደተናገሩት በኢኮኖሚ ያደጉ ሀገሮች በአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ላይ ትኩረት አድርገው በመስራታቸው ውጤት ማምጣታቸውን ጠቅሰው፤ በሀገራችን ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚን ለመገንባት በምናደርገው ርብርብ ውስጥ አምራች ኢንተርፕራይዞች በስፋት መቋቋምና መጠናከር እንዲችሉ አቅደን እየሰራን እንገኛለን ብለዋል፡፡

 

አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች ላይ የምንሰራው ስራ ተጨባጥ ለውጥ እንዲያመጣ በእውቀት ላይ የተመሰረተ ድጋፍ ማድረግ ይገባል ያሉት አቶ ታረቀኝ በተለይም የኢንተርፕራይዞች የማምረት አቅም እንዲያድግ፣ በቴክኖሎጂ እዲታገዙና የገበያ ትስስር እንዲፈጠርላቸው በትኩረት መስራት ይገባል ለዚህም አስፈፃሚ አካላት ተገቢውን እውቀት ይዘው ዘርፉን መደገፍ እንደሚገባቸውም ተናግረዋል፡፡

 

ሚኒስቴር ዴኤታው አክለውም የተቋሙ ደንብ በአዲስ መልክ መጽደቁ በዘርፉ ልማት ላይ የምንሰራውን ስራ ለማሳለጥ ትልቅ እድል እንደሚፈጥር ተናግረው አስፈፃሚው አካል ይህንን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም ለኢንተርፕራይዞች ውጤታማነት ተገቢውን ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባቸውም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

 

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት /ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱልፈታ የሱፍ በበኩላቸው አምራች ኢንተርፕራይዞች ሰፊ የስራ ዕድል እንዲፈጥሩና ለሀገራችን የብልጽግና ጉዞ የድርሻቸውን እንዲወጡ ለማስቻል ተገቢውን ድጋፍ ማድረግ ይገባናል፡፡ ለዚህም የአስፈፃሚው አካላት መብቃት ወሳኝ በመሆኑ ተቋሙ በዘርፉ የድጋፍ ማዕቀፎች፣ መመሪያዎችና የአሰራር ማንዋሎች ላይ ለክልል አስፈፃሚ አካላት በሀገር አቀፍ ደረጃ 3 ማዕከላት የአቅም ግንባታ ስልጠና ማመቻቸቱን ተናግረዋል፡፡

 

ስልጠናው በአዳማ፣ በሀዋሳና በባህር ዳር ከተሞች እየተሰጠ ሲሆን ከሁሉም ክልሎችና ከሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ 500 ሰልጣኞች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

 

 

 

 

Image