Updated and News Updated and News

በሽመና ስራ ስልጠና የወሰዱ ሰልጣኞች ተመረቁ

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ከብሩህ አእምሮ ውስንነት ማዕከል የመጡ 10 ሰልጣኞችን በሽመና ስራ አሰልጥኖ አስመርቋል፡፡

በሽመና ስራ ስልጠና የወሰዱ ሰልጣኞች ተመረቁ

 

EED ህዳር 15/2015 .

 

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ከብሩህ አእምሮ ውስንነት ማዕከል የመጡ 10 ሰልጣኞችን በሽመና ስራ አሰልጥኖ አስመርቋል፡፡

 

በተቋሙ የሽመና ወርክ ሾፕ 21 ቀናት ስልጠናቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ሰልጣኞች በሽመና ስራ ተገቢውን እውቀት ይዘው ወደ ስራ በመግባት ራሳቸውን በኢኮኖሚ ማገዝ እንዲችሉ የተመቻቸ ስልጠና መሆኑ በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ተገልጿል፡፡

 

በምርቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የተቋሙ /ዋና ዳይሬክተር አቶ ጳውሎስ በርጋ እንደተናገሩት በተቋሙ ባሉት ወርክ ሾፖች ለስራ ፈጣሪዎችና ለአምራች ኢንተርፕራይዞች የተለያዩ የሙያ ክህሎት ስልጠናዎችን እየሰጠ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

 

በዚህ ስልጠናም ሰልጣኞች በስልጠና ቆይታቸው ያገኙትን እውቀትና ክህሎት ወደ ስራ እንዲቀይሩ ተቋሙ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ቀጣይነት ባለው መልኩ ተደራሽ እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡

Image