Updated and News Updated and News

የተቋሙ አመራርና ሰራተኞች ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀንን “ሙስናን መከላከል በተግባር” በሚል መሪ ቃል አከበሩ

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት አመራርና ሰራተኞች በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ19ኛ በሀገራችን ለ18ኛ ጊዜ የሚከበረውን የፀረ-ሙስና ቀን “ሙስናን መከላከል በተግባር” በሚል መሪ ቃለ አክብረዋል፡፡

የተቋሙ አመራርና ሰራተኞች ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀንን “ሙስናን መከላከል በተግባር” በሚል መሪ ቃል አከበሩ

 

EED ህዳር15/ 2015 ዓ.ም

 

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት አመራርና ሰራተኞች በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ19ኛ በሀገራችን ለ18ኛ ጊዜ የሚከበረውን የፀረ-ሙስና ቀን “ሙስናን መከላከል በተግባር” በሚል መሪ ቃለ አክብረዋል፡፡

 

የተቋሙ ምክትል ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አብዱልፈታ የሱፍ በመክፈቻ ንግግራቸው እንደተናገሩት ሙስና ልማትን በማዳከም ኢኮኖሚ እንዲገታ፣ የሞራልና የስነ ምግባር ቀውስ እንዲባባስ፣ ሰላምና መረጋጋት እንዳይኖር ህዝብ በመንግስት ላይ እንዲሁም በህግ የበላይነት ላይ አመኔታ እንዲያጣ የሚያደርግ ደንበር ዘለል ባህሪ ያለው ወንጀል መሆኑን አብራርተዋል፡፡

 

አገራችን የዚህ አደገኛ ወንጀል ተጠቂ ናት ያሉት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ይህንን ለመከላከል መንግስት በልዩ ትኩረት እየሰራ ቢሆንም የሙስናን አስተሳሰብም ሆነ ተግባሩን ለማስወገድ  ማህበረሰቡ ከመንግስት ጎን መቆም አለበት ብለዋል፡፡

 

አዳዲስ ኢንተርፕራይዞችን ለማቋቋም በሚደረገው ርብርብ ውስጥ የሙስና አመለካከትና ተግባር እንዳለ የጠቆሙት አቶ አብዱልፈታ ይህንን ለማስወገድ የዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎች በግንባር ቀደምትነት መሳተፍ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡  

 

ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም የአገራችንን የብልጽግና ጉዞ ለማረጋገጥ ኢንተርፕራይዞች ላይ  የምናደርገውን ድጋፍና ክትትል ከሙስና የጸዳ ለማድግ በትኩረት እንሰራለን ብለዋል፡፡

 

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የስነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ዳ/ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ታደሰ ደገፉ በበኩላቸው አገር አቀፍና ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ማዕቀፍ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን  ተቋማዊ አደረጃጀትና አሰራርን ማጠናከር፣ የስነ-ምግባርና የሞራል እሴቶች ግንባታን ማሳደግና ጥናት ላይ የተመሰረተ ሙስናን መከላከል ላይ ቀጣይ ትኩረት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡   

 

ሙስናና ብልሹ አሰራር ለመከላል አገሮች በተናጥል ከሚያደርጉት እንቅስቃሴ በተጨማሪ በጋራ ለመታገል የሚያስችል ዓለም ዓቀፍ ኮንቬንሽን እንዲኖር የመንግስታቱ ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ በውሳኔ ቁጥር 58/422 ኮንቬንሽን እንዲጸድቅ አድርጎል፡፡ የኮንቬንሽኑ ፈራሚ አገራት በጋራ በተወሰነው መሰረት በየዓመቱ ህዳር #30 ቀን የፀረ- ሙስና ቀን በማለት ያከብራሉ፡፡

Image