Updated and News Updated and News

‹‹በኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ዙሪያ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ በትኩረት እየተሰራ ነው!››

‹‹በኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ዙሪያ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ በትኩረት እየተሰራ ነው!››

‹‹በኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ዙሪያ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ በትኩረት እየተሰራ ነው!››

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የ2015 1ኛ ሩብ ዓመት #የእቅድ_አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በአዳማ ከተማ አካሂዷል፡፡


የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱልፈታ የሱፍ በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ እንደተናገሩት #በኢንዱስትሪ_ኤክስቴንሽን_አገልግሎት ዙሪያ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት ተቋማቸው በትኩረት እየሰራ ነው፡

ውጤታማ የኢንዱስትሪ የኤክስቴንሽን አገልግሎት ለመስጠት #አራቱን_የድጋፍ_ማዕቀፎች ባካተተ መልኩ መሰራት እንደሚገባው የገለጹት አቶ አብዱልፈታ በአዲሱ አዋጅ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ለኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በመሰጠቱ ክልሎች ይህን ከግምት ውስጥ በማስገባት እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ም/ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም አሁን ላይ ባለው ተጨባጭ ሁኔታ የአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች ቁጥርና የስራ እንቅስቃሴ በግልጽ ስለማይታወቅ በቀጣይ መረጃዎችን በተደራጀና #በዘመነ_መልኩ ተደራሽ ለማድረግ ተቋሙ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በክልሎች ያለው የስራ አፈጻጸም ክፍተት በማጥበብ ተቀራራቢ አፈጻጸም እንዲኖራቸው የተጀመረውን ክትትልና ድጋፍ አጠናክረን እንቀጥላለን ያሉት አቶ አብዱልፈታ በተለይም #የሊዝ_ፋይናንሲንግ አገልግሎት አፈጻጸም ከክልል ክልል ሰፊ ልዩነት ያለው በመሆኑ ይህንን መቅረፍ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

በዝግጅት ምዕራፍ የነበረውን ክፍተት በመቅረፍ በቀጣይ በተሟላ ሁኔታ የዘርፉን ስራዎች ከአስፈጻሚና ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር በመስራት ውጤታማ አምራች ኢንተርፕራይዞች ለመፍጠር በትጋት መስራት እንደሚጠይቅ ተናግረዋል፡፡

በቅርቡ በሚኒስትሮች ም/ቤት የጸደቀውን አዲሱ #የኢትዮጵያ_ኢንተርፕራይዝ_ልማት_ደንብ በሚመለከት በቅርቡ አስፈላጊውን ግንዛቤ የመፍጠር ስራ እንደሚሰሩም ገልጸው፡፡

Image