Updated and News Updated and News

“የአምራች ኢንተርፕራይዞች ልማት የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ በዘላቂና አስተማማኝ መሠረት ላይ የማቆም አቅም ያለው እንደመሆኑ የድጋፍ ማዕከላችን ሊሆን ይገባል”

“የአምራች ኢንተርፕራይዞች ልማት የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ በዘላቂና አስተማማኝ መሠረት ላይ የማቆም አቅም ያለው እንደመሆኑ የድጋፍ ማዕከላችን ሊሆን ይገባል” አቶ መላኩ አለበል፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት በሐገር ዓቀፍ ደረጃ ለዘርፉ አስፈፃሚዎች ሲሰጥ የቆየውን የአስፈፃሚዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና አጠናቀቀ፡፡

 

በማጠቃለያው ላይ በበይነመረብ በመገኘት መልዕክት ያስተላለፉት የኢንዱስሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል እንደገለፁት የአምራች ኢንተርፕራይዞች ልማት የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ በዘላቂና አስተማማኝ መሠረት ላይ የማቆም አቅም ያለው እንደመሆኑ የዘርፉን ልማት ለመደገፍ የተሠማራን በሙሉ የድጋፍ ማዕከላችን አድርገን መንቀሳቀስ ይገባናል ብለዋል፡፡

 

ጠንካራ የኢኮኖሚ አቅም ከገነቡ ሐገሮች ጀርባ ጠንካራ የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት አለ ያሉት ሚኒስትሩ ይህን ተጨባጭ ዓለማዊ ሁኔታ መሠረት በማድረግ የሐገራችንን ኢኮኖሚ ለመገንባት የአምራች ዘርፉን መደገፍ የግድ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

 

እንደሚኒስቴር መስሪያ ቤት የአምራች ዘርፉን ለመደገፍ የተለያዩ ፖሊሲና ስትራቴጂዎችን የማሻሻልና የማዘጋጀት ስራዎች በስፋት እየተከናወኑ መሆኑን የገለፁት አቶ መላኩ ከዚሁ ጎን ለጎን ለአምራች ኢንዱስትሪው ወሳኝ የሆኑ የገበያ አመራጮችን በሐገር ውስጥ በስፋት የማፈላለግ ስራዎች በውጤታማነት እየተከናወኑ እንደሚገኙ አብራርተዋል፡፡

 

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት /ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱልፈታህ የሱፍ በበኩላቸው አስፈጻሚ አካላት በዘርፉ ልማት ተጨባጭ የሆነ ውጤት ለማስመዝገብ እንዲችሉ በዘርፉ ልማት ዙርያ በቂ ግንዛቤን ማስያዝ ማስፈለጉን እንደመነሻ በመያዝ ሐገራዊ ስልጠናው መዘጋጀቱን አስታውሠው በግንዛቤ ማስጨበጫው መነሻነት በላቀ መነቃቃትና የግንዛቤ አቅም አምራች ኢንተርፕራይዞችን መደገፍ እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

 

በሐገራዊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ 500 በላይ አስፈፃሚዎች የተሳተፉ ሲሆን በግንዛቤ ስልጠና መድረኩ የማምረት አቅም አጠቃቀም፣ የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን፣ የካይዘንና ስራ አመራር፣ የገበያና የክላስተር ማዕከላት አስተዳደርን ጨምሮ 10 ያህል የስልጠና ርዕሠ ጉዳዮችን ያካተተ ነበር፡፡ ስጠናዎቹም በአዳማ፣ ባሕርዳርና ሐዋሳ ከተሞች ተሠጥተዋል፡፡

Image